(አዲስ አበበ ሀምሌ 1/2017 ዓ.ም.) በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተደረገ የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ኢንሼቲቭስ የሱፐርቪዥንና ድጋፋዊ ክትትል የማጠቃለያ ሪፖርት ሰኔ 30/ 2017 ዓ.ም በክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) መሪነት በዋናው መስሪያ ቤት ቀርቦ ነበር የተገመገመው፡:
የሱፐርቪዥኑ ልዑካን ቡድኑ ወደየ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከመውጣቱ ፊት በተደረገው የስራ መመሪያና ተልዕኮ መሰረት፤ ተጨማሪ መረጃ ለሚቀጥሉ ዉሳኔዎች ለማቅረብ፤ እንደሀገር የተያዘውን የሰብአዊ ድጋፍ ሉአላዊነት ዕቅድ ምን ያህል ተፈጻሚ እየሆነ እንዳለ እና ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ወይም የሰብአዊ ድጋፍ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባራዊ አፈጻጸም መገምገምን አላማ ያደረገ እንደነበረም ተገልጾል፡፡
በዚህ መሰረት የሰብአዊ ድጋፍ ሉአላዊነት የግብ ስኬቶችን፤ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ፓኬጆችና የጽንሰ ሀሳቦች መለኪያዎች ያሉበትን ደረጃ፤ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ክምችቶች ዕቅድ፣ አያያዝና አፈጻጸም ነባራዊ ሁኔታ፤የአደጋ ፈንድ አመራር፣ አሰባሰብና አያያዝ፤ደረጃቸውን የጠበቁ መጋዘኖች ልየታ፣ አያያዝና አጠቃቀም፤ የቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ዝግጁነት፣አሰራር፣ አደረጃጀትና አመራር፤ የቤተሰብ ሀላፊነትና የማህበረሰብ አጋርነት አስራርና አተገባበር ላይ ያተኮረ ሪፖርት እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ፍኖተ-ካርታ አፈጻጸም (መግባባት፣ ማጥራት፣ ማዘጋጀት፣ ማቀናጀትና ማሸጋገር) ዙሪያ የተደረጉ አፈጻጸሞችንም የደሰሰ ሲሆን ክልሉ የሚገኝበት ውጤት (ስኮርድ ካርድ) በተዘጋጀው ቼክ ሊስት አማካይነት ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የወጡ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮችንም ለመለየት ምቹ ዕድል እንደፈጠረም ተጠቁሟል፡፡
በሱፐርቪዥኑ የኮሚሽኑ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በቡድን ተልዕኮቸውን ተቀብለው የሀገራዊ ስሜት ተላብሰው የተሰማሩት ሲሆን ልዑካኑ ያቀረቡን ሪፖርትና የነበራቸውን ተነሳሽነት በማድነቅ ኮሚሽነሩ ለተልዕኮው ተሳታፊዎች በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም( ዶ/ር) በአጠቃላይ የሪፖርቱ ውጤት በመነሳት አጥጋቢ ስራ መሰራቱን፤ ለክልሎችንና ለከተማ አስተዳደሮችም መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን፤ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የዕቅድ አፈጻጸም አዎንታዊ ዉጤት አመላካችና የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ለቀጣይ በሪፖርቱ የተለዩትን ክፍተቶች ለመሙላት በካውንተር ዳወን (Counter down) ስርአት በመከተል ምንም የሚባክን ጊዜ ሳይኖረን መፍጠንና መፍጠር እንደሚጠበቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡



