የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮችና የብልፅግና ፓርቲ ህብርት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

በቀን 23/2017 ዓ.ም/አሶሳ/ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ሉዓላዊነት! በሚል መሪ ሃሳብ የኮሚሽኑ የብልፅግና ፓርቲ ህብረት የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሃሳብ መፅሔት የሚያዚያ/2017 እትም ላይ መነሻ አድርገው ውይይት አደርገዋል፡፡

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን መሸፈን ለራስና ለአገር ክብር፣ ነጻነትና ሉዓላዊንት ዘብ መቆም በመሆኑ የልመናንና የተረጂነትን አመላካከት የማይሸክምና ለአደጋ ስጋት የማይበገር ህዝብና ማህበረሰብ ለመገንባት በአመለካከት ለውጥ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊን ቁጥር በማጥራት፣ አቅምና ምርትን በማጠራቀምና ሊገጥሙ ለሚችሉ አደጋዎች ቀድሞ ለመዘጋጀት በክልሉ አቅም ለመሸፈን ኮሚሽኑ የእርሻ ስራ ማከናወኑ ትልቅ ስኬት እና ለታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ መሆኑና በማድነቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አባላቱ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *