በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጣሊያን ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በኡራ ስደስተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ስደተኞች የ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዛብ ድጋፍ አደረገ።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጣሊያን ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በኡራ ስደስተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ስደተኞች የ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዛብ ድጋፍ አደረገ።

‎‎በጽ/ቤቱ የሱዳን ስደተኞች አስተባባሪ አቶ ተመስገን አምሳሉ እንዳሉት ማህበሩ ከጣሊያን ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በዑራ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለሚገኙ ስድተኞች የ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ‎

ለስደተኞቹ የተሰጠው ድጋፍም አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን እንዲያሟሉ ታስቦ መሆኑን አቶ ተመስጌን ተናግረዋል። ‎

በዑራ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ በአጠቃላይ ከ500 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በድጋፉ ተጠቃሚ እንዳሆኑም አስተባባሪው አስታውቀዋል።

የተሰጠው የገንዘብ ድጋፍም 164 አባወራዎች እና 362 እማዋራዎችን ጨምሮ የአካል ጉዳተኞችን እና አቅመ ደካሞችን በማካተት ተደራሽ እንደተደረገም ነው አቶ ተመስገን ያብራሩት።

‎‎የድጋፉ ተጠቃሚ ስደተኞችም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

‎‎እስካሁንም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በዓይነት እና በገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግላቸው የቆየ መሆኑንም ስድተኞቹ ገልጸዋል። ‎

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *