የድባጤ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት በወረዳዉ አሰተባባሪነት ለተረጂነት ቅነሳ ፈንድ የሚሆን 20 ሄክታር የአኩሪ አተር የእርሻ ሰራ አሰጀመረ።

ድባጤ:-ሐምሌ 17/2017 የድባጤ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በወረዳዉ አስተባባሪነት ለተረጂነት ቅነሳ ፈንድ የሚዉል የአኩሪ አተር የእርሻ መሬት የወረዳዉ አመራሮች በተገኙበት ጎብኝት ተደርጓዋል።

በጉብኝቱ ወቅት መንግስት ለተረጂነት ቅነሳ የሚሆን ፈንድ 20 ሄክታር መሬት በአኩሪ አተር ለመዝራት መጠነ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ተገኘ ገልጸዋል።

በወረዳ መንግስት አስተባባሪነት ከሚታረሰዉ 20 ሄክታር አኩሪ አተር እርሻ 11.5 ሄክታር በዘር መሸፈኑን የገለጹት የወረዳዉ ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ መሀመድ ደረሰ ናቸዉ።

ተረጃነትን መቀነስና የእያንዳንዱን ዜጋ አቅም ማሳደግ የምግብ ዋስተናን ያረጋጋጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የድባጤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ከሰሰ ገልጸዋል።

የድባጤ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የምግብ ዋስትና እና አደጋ ስጋት ቡድን መሪ አቶ ሽባበዉ ቡሽን በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ በሚከሰቱ አደጋዎች ምክኒያት ለተጎዱ ወገኖች የሚውልና በራስ አቅም ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር አላማ አድርጎ ወረዳዉ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

በወረዳዉ መንግስት አስተባባሪነት ከሚታረሰዉ ከተረጂነት ቅነሳ እርሻ ዉጭ 40 ሄክታር እርሻ በቀበሌዎ እየተሰራ መሆኑን ጭምር ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *